Fana: At a Speed of Life!

6ኛ ዙር ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛ ዙር ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

ዝግጅቱ ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመድሀኒዐለም ትምህርት ቤት አደባባይ ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን መሪነትና አዘጋጅነት በተካሄደው ከተማ አቀፍ የማህበረሰብ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር ፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ይታያል ደጀኔ እና የካቢኔ አባላት ፣ነዋሪዎች ፣ አርቲስቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል ።

ዝግጅቱ “ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ!” በሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል።

ቀጣይ 7ኛውን ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያስተናግደው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከአዲስ ከተማ ችቦውን ተረክቧል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.