Fana: At a Speed of Life!

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በርካታ ጀግኖችን ያፈራ ዞን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በርካታ ጀግኖችን ያፈራ ዞን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፥ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በተኙበት የሻምቡ ባኮ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ምረቃ እና የሻምቡ ሀገምሳ የመንገድ ግንባታን የማስጀመር ስነስርአት በሻምቡ ከተማ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢው ለሀገር ግንባታ የድርሻውን ሲሰጥ ቢቆይም ተገፍቶ ወደ ሗላ ቀርቷል ብለዋል።

አሁን በአካባቢው ያለውን እምቅ ሀብት ለማውጣት እና ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል።

ወለጋ የሚጠበቅበትን እያደረገ፥ ግብር እየከፈለ፥ መብራት ለሀገር እያመነጨ ከልማቱ ግን ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

አሁን ግን መንግስት የድርሻውን መወጣት ስለጀመረ ህዝቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ለሀገር ግንባታ የተሳሰረ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢውን ይበልጥ በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ወሳኝ ናቸውም ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ከበርካታ ችግሮች ጋር  እየታገለ እና እያሸነፈ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.