Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት 90 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለው የመስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት 90 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ።

በግንባታ ስራ ላይ ለተሳተፉ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ስምንት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን 90 በመቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።

ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

የመስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት 1 ሺህ 400 ተሽከርካሪዎችን ማቆሚያ፣ 24 የመገልገያ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያና ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል ነው።

የከተማው አስተዳደር በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ ለተሳተፉ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ዛሬ የምስጋናና የምሳ ግብዣ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት በከተማው እየተገነቡ ያሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች  በጥሩ አፈጻጸም ላይ ላይ ይገኛሉ።

በከተማዋ አሁን በግንባታ ላይ ካሉት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በቀጣይ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጀመሩ ተናግረዋል።

በከተማዋ ለሚሰሩት የተለያዩ የልማት ስራዎች ከመንግስት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ምክር ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

አሁን ላይ መንግስት የግል ዘርፉን በሚያሳትፍ መልኩ እየሰራ በመሆኑ ከመንግስት ጋር ተባብረን እንሰራለንም ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ መለሰ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.