Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የምርጫ 2013 የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡

የዕውቅና መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፓርቲያችን ብልጽግና የአገራችንንና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት የገመገመ፣አገራችንን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በውል ለይቶ ትክክለኛ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ፣ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝቦች በእኩል አካቶና አቅፎ የማታገያ ሜዳ ያመቻቸ፣በሚሊዬን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን በአባልነትና በደጋፊነት ከጎኑ ያሰለፈ፣በለውጥ ውስጥ የተወለደ፣ለለውጥ የሚተጋ፣የተስፋ ብርሐን የሰነቀ የዛሬና የነገ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ ፓርቲው በምርጫ ወቅት የሚጠቀምበትን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትን ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም የፓርቲው መወዳደሪያ ምልክት እየበራ ያለ አምፖል ሆኗል፡፡

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.