Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከተማ በማህበረሰብ ልማት ፈንድ የተሰራ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት አስመረቀ።

የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተውታል።

የተመረቀው ፕሮጀክት በድሬዳዋ ከተማ 700 የገንደ ሪጌ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ፓዮኔር ከተባለ የሲሚንቶ ኩባንያ ነው።

የማዕድን ኩባንያዎች ማዕድንን የሚያለሙበት አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል የማህበራዊ ልማት ክፍያ ነው።

በቀጣይም በ4 ሚሊየን ብር የመጠጥ ውሃ እና ሌሎች አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.