Fana: At a Speed of Life!

ሰማሪታንስ ፐርስ በትግራይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኞች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰማሪታንስ ፐርስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትግራይ ክልል ሠብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ዓልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡

ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤቱ ከሚገኝበት ሰሜን ካሮላይና ግዛት ቡን ከተማ በራሱ የዕቃ ጫኝ አውሮፕላን የላከው 310 ኩንታል የምግብ ቁሳቁስ ዛሬ መቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ተራግፏል፡፡

አልሚ ምግቡ በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ሕጻናት፣ ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች የሚውል እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ድጋፉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገብረሕይወትና የካቢኔ አባላት ተረክበዋል።

ሰማሪታንስ ፐርስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ምዝገባ ቁጥር 4046 ተመዝግቦ የበጎ አድራጎት ስራውን በመከወን ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.