የሀገር ውስጥ ዜና

ከአዲስ ቅዳም ወደ እንጅባራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሽ ተገልብጦ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ

By Tibebu Kebede

February 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ ቅዳም ወደ እንጅባራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሽ ተገልብጦ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው በተለምዶ አድጓሚ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ መሆኑን የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአዲስ ቅዳም ጤና ጣቢያና በእንጂባራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ቦታው ቁልቁለትና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ፍጥነት በመቀነስ እንዲያሽከረክሩም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!