Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በቢሾፍቱ ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሚና ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሃገራዊ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ሚናቸውን እንዴት መወጣት እንዳለባቸው የሚያመላክት እንደሆነም ተገልጿል።

የሃገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ስራ አስፈጻሚ ወጣት ሜሮን አለሙ÷ ኅብረቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረ ጀምሮ በሃገሪቷ ተከስተው ያለፉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብና በሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግራለች።

ወረርሽኞች፣ የአንበጣ መንጋና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ ከሕዝቡ ጎን በመሆን ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሳለች።

እነዚህን መሰል የኅብረቱን ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠል የውይይት መድረኩ ማስፈለጉንም ገልጻለች።

በውይይቱ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንቶች ታድመዋል።

ኅብረቱ በውይይቱ ማጠናቀቂያ ቀጣይ ስራዎቹን አስመልክቶ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣ ከመርሃ ግብሩ ማወቅ መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.