Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-እስራኤል የፖለቲካ የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ3ተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮ-እስራኤል የፖለቲካ የምክክር መድረክ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በበይነ መረብ ተካሂዷል።

የምክክር መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም የፖለቲካ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በምክክር መድረኩ  የሁለቱ አገራት መንግስታት በግብርናው ዘርፍ በተለይም በአቮካዶ ምርት እና የአትክልት እርባታ ፣ የበይነ መረብ ደህንነት፣ ኢንቨስትመንት፣ የህዋ ሳይንስ፣ የሀይል አቅርቦት እንዲሁም ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ይፋዊ ጉብኝቶች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ከዚያም ባለፈ በምክክር መድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በተደረጉ ለውጦች፣ በቅርቡ ሊካሄድ ስለታሰበው ብሄራዊ ምርጫ፣ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ህግን የማስከበር ዘመቻና በክልሉ መንግስት እያካሄዳቸው ስለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባራት ዙሪያ ገለፃ ተደርጓል።

በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ በኢትዮጵያ በኩል ችግሩን በሰላም ለመፍታት እየተደረገ ስላለው ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እየተካሄደ በሚገኘው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ድርድሩን የማስቀጠል አቋም በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል።

በእስራኤል የሚገኙ በኢትዮጵያ የተያዙ የሀይማኖት ቦታዎች እድሳት ዙሪያና ኢትዮጵያ በእየሩሳሌም የባህል ማዕከል ለመክፈት እንደምትፈልግ ተገልፆ ውይይት እንደተካሄደባቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.