Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በህ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው 2 ሚሊየን ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት ለሸማች ማህበራት እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሞኑ በግለሰብ መጋዘን በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው 2 ሚሊየን ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ሸማች ማህበራት እየተሰራጨ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ ጎን በአንድ ግለሰብ መጋዘን ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 2 ሚሊየን ጀሪካን የፓልም የምግብ ዘይት በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙ የሚታወስ ነው።

የተያዘው የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሸማች ማህበራት አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት በዛሬው ዕለት የማሰራጨት ስራው ተጀምሯል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተያዘው የዚህ ዘይት መሰራጨት በከተማዋ የሚስተዋለውን እጥረት ያቃልለዋል ብለዋል።

በቀጣይም በክፍለ ከተማው መሰል የፍጆታ እቃዎችን በመጋዘን የሚያከማቹ ግለሰቦችንና ተቋማትን ለመቆጣጠር የተደራጀው ልዩ ግብረ ኃይል መንግስት በድጎማ የሚያስገባቸውን መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በሕገ ወጥ መንገድ በማከማቸት እና የአቅርቦት እጥረት በመፍጠር የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳልም ነው ያሉት።

ህብረተሰቡ በየትኛውም አካባቢ የፍጆታ ሸቀጦችን የሚያከማቹ አካላትን እና ግለሰቦችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.