Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ለመተከል ተፈናቃዮች የአልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ለመተከል ተፈናቃዮች በ2 ሚሊየን ብር ወጪ የአልሚ ምግብ ድጋፍ አደረገች።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ምክትል ፕሬዚዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው እንደገለፁት÷ ድጋፉ በመተከል ዞን በተፈጠረው አለመረጋጋት ተፈናቅለው በ6 ወረዳዎች ለሚገኙ ዜጎች በተለይ ደግሞ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ህጻናት ነው፡፡
በአጠቃላይ 425 ካርቶን አልሚ ምግብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለ5 ሺህ 100 ህጻናት ተደራሽ እንደሚሆን መጋቢ ለወየሁ ተናግረዋል።
በቤተክርስቲያኗ በኩል የተደረገው ድጋፍ ከአልሚ ምግብ በተጨማሪ የከፋ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት አልባሳትም ያበረከተች ሲሆን በቀጠናው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎች የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል።
በድጋፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ፤የተደረገው ድጋፍ ህጻናት በከፋ ችግር ውስጥ ባሉበት ሰዓት መደረሱ የተሻለ ዜጎችን እንዲታደጉ አድርጓል ብለዋል።
ተፈናቅለው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ መንግስት ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.