Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጃፓን በመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና ጃፓን በመሠረተ ልማት ሥራዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ በ2ኛው ኢትዮ ጃፓን የመሰረተ ልማት ኮንፈረንስ ላይ በአዲስ አበባ ተፈርሟል።

በኮንፈረንሱ ላይ የሁለቱ ሃገራት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ሃገር በቀል ተቋራጮች እና ከጃፓን የመጡ ከ20 በላይ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ ኮንፈረንሱ ጃፓን በዘርፉ ያላትን የዳበረ ልምድ ለኢትዮጵያ የምታጋራበትና በጋራ የምንሰራበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

የጃፓን የመሬት፣ የመሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርትና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ኖቡህዴ በበኩላቸው፥ የጃፓን ባለሃብቶችን በማሳተፍ ዘርፉን ለመደገፍና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ በትኩረት ሊሰራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.