Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሞተር ጥገና በኋላ ለሚደረግ የደህንነት ፍተሻ የደህንንት ማረጋገጫ መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል የGEnx-1B የአውሮፕላን ሞተር ከጥገና በኋላ ለሚደረግ የደህንነት ፍተሻ እና ሙከራ ማረጋገጫ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

አየርመንገዱ በተጨማሪም የደህንንት ማረጋገጫ በመስጠት ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው አየር መንገድ ለመሆን መብቃቱን ነው የገለጸው።

ከአሁን ቀደም የአውሮፕላን ሞተሮቹ በአውሮፕላን ጥገና ባለሞያዎቻችን ከተጠገኑ በኋላ ለሙከራ እና የፍተሻ ማረጋገጫ ለማግኘት እንግሊዝ ወደሚገኘው ጀነራል ኤሌክትሪክ የጥገና ማዕከል ይላኩ እንደነበር ጠቅሷል፡፡

ይህ ሁኔታ ከአሁን በኋላ የአውሮፕላኖቹ ሞተሮች በራሱ ባለሞያዎች ተጠግነው ደህንነታቸው ተፈትሾ፣ አውሮፕላን ላይ ተገጥመው ለበረራ ዝግጁ የማድረግ አቅም እንዲኖር ያስችለኛል ብሏል አየርመንገዱ።

ይህንን ዓይነት ከጥገና በኋላ የሚደረግ ሙከራ በመስጠት የአየር መንገዱ የጥገና ክፍል ከዓለም ስድስተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ መቻሉንም ከአየርመንገዱ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.