Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና ዳይሬክተር ቼፕቶ አሞስ ኪፕሮኖህ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በትብብር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከዋና ዳይሬክተሩ ቼፕቶ አሞስ ኪፕሮኖህ ጋር ተወያዩ ፡፡

ሚንስትሩ መስሪያ ቤቱ እያከናወናቸው ስለሚገኙ ዋና ዋና የልማት እንቅስቃሴዎች በዝርዝር ገለጻ አድርገውላቸው ተወያይተዋል ፡፡

በተለይም ደግሞ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በትብብር ስለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች መክረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩም በግንባታ ላይ የሚገኘውን የመቀሌ የንጹኅ መጠጥ ውሃንና ሌሎች የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት በተመለከተም ማብራሪያ ጠይቀው ከሚንስትሩና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ምላሽ አግኝተዋል፡፡
በዚህም መሰረት በልማት ባንኩ የገንዘብ በትብብር እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰትም ግንባታውን በሚፈለገው ፍጥነት ለማድረግ እክል መፍጠሩንም አንስተውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም የመቀሌ ከተማን የንጹኅ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን በተመለከተም በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው ህግን የማስከበር ዘመቻ የተጠበናቀቀ በመሆኑና አከባቢው ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እየተመለሰ በመሆኑ የፕሮጀክቱ ግንባት እንደሚቀጥል አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ልማት ባንክና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በትብብር ሊሰሯቸው የሚችሉባቸው መስኮች በመለየት ሚንስትሩ ገለጻ አድርውላቸዋል፡፡

በተለይም በኢነርጂው ዘርፍ መንግስት ያካሄደው ሪፎርም በዘርፉ ለማልማት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ ባንኩ በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ሃይል ለማቅረብ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዝም ሚንስትሩ ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ የውይይት ግዜም የህዳሰሴውን ግድብ የግንባታ ሂደትና በሶስቱ ሃገራት መካከል ሲደረግ የነበረውን ድርድር አሰመልክተው ለዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋቸዋል፡፡

ባሳለፍነው የፈረጆቹ አመት የህዳሴው ግድብ የመጀመሪው የውሃ ሙሌት መከናወኑ ሱዳንን ከከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ የታደገ መሆኑን በመጥቀስ የግድቡ መገንባት ለሱዳን የሚያስገኘው ጠቀሜት ከፍተኛ ሆኖ ሳለ ግን ወደ ስምምነት ለመድረስ ፍላጎት የላቸውም ብለዋል፡፡

አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትም ለግድቡ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ለማበደር ፍቃደኞች አለመሆናቸውን አንስተው ይሁንና ግን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ገንዘብ ገንብተው ግድቡን 78.3 በመቶ ማድረስ መቻላቸውን አስተድረተዋል፡፡

ኢትዮጵያም ግድቡን አጠናቃ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን በሃይል ታስተሳስራለች ብለዋል፡፡

ከዚህም አኳያ ባንኩ ለኢትዮጵያና ኬንያ ትስስር ስላደረገው የገንዘብ ብድርም አመስግነዋል::

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.