Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በቤልጅየም ከፍላንደር ኢንቨስትመንት እና ንግድ ኤጀንሲ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከፍላንደር ኢንቨስትመንት እና ንግድ ኤጀንሲ ተወካይ ጋር በበይነ መረብ ተወያዩ።

በዚህ ወቅትም ለኤጀንሲው የአፍሪካ ተወካይ ለሊሴ ቤትጀስ በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የገበያ ዕድሎችን በተመለከተ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት፣ አሜሪካ ለአፍሪካ የሰጠችው የገበያ ዕድል እና የአውሮፓ ህብረት ለታዳጊ ሃገራት የሰጠው ከኮታና ከቀረጥ ነጻ መብት እንዲሁም በሃገር ውስጥ ያለው ሰፊ ገበያና የሰው ኃይልን ታሳቢ በማድረግ ቀደም ሲል ከክልሉ መጥተው በኢትዮጵያ ከተሰማሩት በተጨማሪ ሌሎችም መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የኤጀንሲው ተወካይ ለሊሴ ቤትጀስ በበኩላቸው የኮኖና ቫይረስ ስጋት ሲቀረፍ በኢትዮጵያ የቢዝነስ ጉብኝት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.