Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ወራት በነዳጅ ላይ የታየውን ጭማሪ ከግምት በማስገባት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ዛሬ የታሪፍ ማሻሻያውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በነዳጅ ላይ የ5 ነጥብ 90 ብር ጭማሪ መኖሩን ከግምት በማስገባት የነዋሪውን የኑሮ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በሚኒ ባስ፣ ሃይገርና መካከለኛ አውቶብሶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

በማሻሻያው ላይ ጭማሪ ያልተደረገባቸው መስመሮች መኖራቸውም ተገልጿል።

በዚህም በሚዲ ባስ ወይም የሃይገርና መካከለኛ አውቶብሶች ላይ የተሻሻለው ታሪፍ እስከ 8 ኪሎ ሜትር 3 ብር የነበረው ባለበት ሲቀጥል ከ8 ኪሎ ሜትር በላይ ያሉት ታሪፎች ላይ የ1 ብር ጭማሪ ተደርጓል።

በሚኒ ባስ ከኮድ 1- 3ን በተመለከት እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 2 ብር የነበረው ባለበት ይቀጥላል።

ከ 2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር 4 ብር የነበረው 4 ብር ከ50 ሳንቲም፣ ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 6 ብር የነበረው 6 ብር ከ50 ሳንቲም፣

ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር 8 ብር የነበረው 9 ብር  እንዲሁም ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 10 ብር የነበረው 11 ብር ሆኗል፡፡

ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው 13 ብር፣ ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 13 ብር የነበረው 15 ብር ከ50 ሳንቲም እንዲሁም ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 15 ብር የነበረው 17 ብር ከ50 ሳንቲም እንዲሆን ተወስኗል።

በሸገር አንበሳ እና ድጋፍ ሰጪ የብዙሃን ትራንስፖርቶች ላይ የከተማ አስተዳደሩ በአመት 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ድጎማ በማድረግ በነበሩበት ዋጋ እንዲቀጥሉ ተደርጓል።

በሃይማኖት ኢያሱ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.