የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ ጠ/ሚ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

February 17, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ማርክ ሩት በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ነው የተወያዩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በውይይቱ ወቅት በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መምክራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኔዘርላንድስ ጋር በዲፕሎማሲ፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት በኩል ያላት የቆየ ግንኙነት ለቀጣይ ግንኙነት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!