Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የነጻ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት በነጻ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ የሚሰጠው ከየካቲት12 ቀን እስከ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ተብሏል፡፡

ቢሮው ከጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከፕሮጀክት ሃረር ኢትዮጵያና ከስማይል ትሬን ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር አገልግሎቱን እንደሚሰጥ ገልጿል።

ለከንፈር መሰንጠቅ እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለላንቃ መሰንጠቅ ከ2 ዓመት እድሜ ጀምሮ ችግር ያለባቸውን ህጻናትና አዋቂዎች የነጻ ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የቢሮው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.