የሀገር ውስጥ ዜና

በስድስት ወራት ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ቤቶችን ተገንብተዋል – የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

By Abrham Fekede

February 17, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች በስድስት ወራት ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ቤቶችን መገንባታቸውን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን ያለው የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዘርፍ የዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሀረር ከተማ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው።

ሚኒስቴሩ 82 ሺህ 652 ቤቶች ለመገንባ አቅዶ 40 ሺህ 339 ቤቶችን መገንባቱን ነው የገለጸው፡፡

በማህበር ቤት 5 ሺህ 580፣ በሪልስቴትና በግለሰቦች 4 ሺህ 616፣ በግለሰብ የተገነቡ ቤቶች 24 ሺህ 139፣ በመንግስት 20/80 ፕሮግራም 528፣  በመንግስት 40/60 ፕሮግራም 3 ሺህ  550 እና በኪራይ ቤቶች  1 ሺህ 926  ቤቶች መገንባታቸውን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ አፈጻጸሙ ከታቀደው አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ጠቁሟል።

በግማሽ ዓመቱ ለ21 ሺህ 476 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።