Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ወንዝ የሚያስከትለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ጋር የአዋሽ ወንዝ የሚያስከትለውን የጎርፍ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ፡፡

ሚኒስትሩና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የአዋሽ ወንዝ ቀደም ባሉት ዓመታት በተደጋጋሚ ጊዚያት በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላት በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በቁም እንስሳት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ላይም ተወያይተዋል፡፡

ችግሩን ለመከላከል ክልሉ ከፌዴራል መንግስት እና ከልማት አጋሮች ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አቶ አወል አርባ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ጉዳቱ የደረሰባቸውን ነዋሪዎች በዘላቂነት የማቋቋም ስራዎችም መልካም ውጤት ማስገኘታቸውንም በውይይቱ አንስተዋል፡፡

አቶ አህመድ በበኩላቸው የአዋሽ ወንዝ በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የቅድመ መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ከክልሉ ጋር በመተባበር ከአዋሽ ወንዝ ጋር በተያያዘ የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከልም አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.