Fana: At a Speed of Life!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን የምግብ ዘይት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን ፈሳሽ የምግብ ዘይት ተያዘ።

መንግስት በድጎማ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሰራም ህገወጦች ባቋራጭ ለመክበር የፍጆታ እቃዎችን በመደበቅና በማከማቸት ነዋሪውን ለችግር እያጋለጡ ይገኛል ብሏል የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት።

የከተማ አስተዳደሩም የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር እያደረገ ባለው ድንገተኛ ፍተሻም በዛሬው እለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን (132ሺህ ሊትር) የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው ያለው።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ከህብረተሰብና የፀጥታ ሀይሎች ህገወጦችን ለማጋለጥ ያደረጉት ክትትልና ቁጥጥር የሚመሠገን ሲሆን በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን የማጋለጡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነው ሲል አስታውቋል።

ፖሊስም በጉዳዩ ዙሪያ ማስረጃዎችን ሰብስቦ ምርመራ በማድረግ ላይ ሲሆን ህብረተሰቡ በከተማዋ የፍጆታ እቃዎችን ሆን ብለው በመደበቅ እና በማከማቸት ሰውሰራሽ እጥረት በመፍጠር የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.