የሀገር ውስጥ ዜና

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በትራንስፖርት መሪ ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By Meseret Awoke

February 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ቼፕሮ አሞስ ኪፕሮኖህ ጋር በቀጣይ 10 ዓመታት በሚተገበረው የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ ተወያይተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋር ሆኖ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለይም ባንኩ በኢትዮጵያ ለልማት ሥራ ከሚያዉለው 1.65 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዉስጥ 31% በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ እንደሚዉል ይታወቃል።

በሌላ በኩል በልማት ባንኩ ድጋፍና ብድር በሚሰሩ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተግባራዊነት ላይ በሚታዩ አንዳንድ የአፈፃፀም ችግሮች ዙሪያም ተወያይተዋል።

የልማት ባንኩም የተለመደውን አጋርነት አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ከሚኒስትሯ ጋር ተወያይተዋል።

ቀጣይ በሚኖሩ የልማት ስራዎች በተለይም ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለዉን የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድን ለማሳካት ከባንኩ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!