Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክርቤት መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር ስምንተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው መደበኛ ጉባዔ አጀንዳዎች የምክር ቤቱን 20ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ እና አስቸኳይ ጉባዔ ቃለጉባዔ ገምግሞ ያጸድቃል፡፡

ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም፣ የ2012 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት፣ የከተማ አስተዳደሩን ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገምግሞ ያጸድቃል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን የመሬት ካሳ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴን መሰየም እና ሹመቶችም ይካሄዳሉ ተብሎ  እንደሚጠበቅ አብመድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.