Fana: At a Speed of Life!

የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት የተከሰሱበትን የሙስና ወንጀል አልፈጸምኩም ብለው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የተከሰሱበትን የሙስና ወንጀል አልፈጸምኩም ብለው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ።

ተጠርጣሪው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በተከሰሱበት 2 የሙስና ወንጀል ክሱ በችሎት ከተነበበላቸው በኋላ ጠበቆቻቸው መቃወሚያ የለንም ያሉ ሲሆን አቶ ሙሉጌታም ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲሉ የእምነት ከህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ህግ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያስረዱ ምስክሮቼን ላሰማ ማለቱን ተከትሎ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 7 እና 8 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በቦሌ ክፍለከተማ ያለአግባብ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት በመውሰድ እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ደግሞ 11 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ወረራ በማድረግ በሚል ሁለት የሙስና ክስ ነው የተመሰረተባቸው፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.