Fana: At a Speed of Life!

የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታዎች ተጠናቀው ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ሲከናወን የቆየው የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታዎች ተጠናቀው ተመረቁ፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የተማሪዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ‹‹የክፍል-ተማሪ›› ጥምርታን ለማሻሻል በማሰብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ እንዲደረግ ልዩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል፡፡
በዚህም በአስሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙና በተመረጡ 150 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 721 የመማሪያ ክፍሎችና 230 በላይ የመመገቢያ አዳራሾች ተገንብተው መመረቃቸውን ከአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለማስፋፊያ ግንባታውም 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.