Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ነፃ የምክር አገልግሎት ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መምከሩን አስታወቀ፡፡

በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከህዝቡ ጋር በቅርርቦሽ እየሰራ እንዳለም ገልጿል፡፡

ይህንንም ለማጠናከር የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የነፃ የምክር አገልግሎት ኮሚቴ መቋቋም አስፈልጓል ነው ያሉት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጀነራል ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ፡፡

ኮሚቴውም የሀይማኖት አባቶች፣ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ምሁራን እና የህብረተሰብ ተወካዮችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ዋናው ስራውም የህዝብና የፖሊስ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የህግ የበላነት እንዲከበር እና ህዝቡ በፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ቅሬታ መፍታት ነው ብለዋል ጀነራል ኮሚሽነሩ፡፡

እስከ ቀበሌ ድረስም ከህብረተሰቡ ጋር የሚሰራ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

የፖሊስ ኮሚሽኑ ጀነራል ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለስራው ተግባራዊነት የፖሊሶች ስነምግባር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሰራሩ የፖሊስ ስራን ከህብረተሰቡ ለማስተሳሰር እና ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ብለዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.