የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጋር የሃገራቱን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

February 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅት የሁለቱን ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆኑ ሃገራት መካከል አንደኛዋ መሆኗን ጠቅሰው፥ የጀርመን የንግድ ተቋማት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲቀጥሉ አበረታተዋል፡፡

የሃገራቱን የቆየ አጋርነት ያነሱት ሚኒስትሩ ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍም አድንቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና መልሶ ግንባታ ሂደትን በተመለከተም ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!