Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ባንክ 17 ፓትሮል ተሽከርካሪዎችን ለአዲስ አበባ መስተዳድር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ 17 ፓትሮል ተሽከርካሪዎችን ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አስረከበ፡፡

ባንኩ በአዲስ አበባ ከተማ በትራንስፖርት እና በመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ትግበራ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሽከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡

ዛሬ ርክክብ የተደረገባቸው 17 ፓትሮል ተሽከርካሪዎችን የፕሮጀክቱ አንዱ አካል መሆናቸውን ዳይና ገልጸዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የዓለም ባንክ ባለፉት ዓመታት በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣በትምህርት፣በጤና እና በምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃግብሮች በርካታ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ባንኩ ዛሬ ያደረገው የተሽከርካሪ ድጋፍም የከተማዋን የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥ እንዲሁም  የሰላም እና ጸጥታ ስራን በይበልጥ ለማረጋገጥ  እንደሚያግዙ አቶ ጥራቱ መጠቆማቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.