Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ሕብረት ከ3 ሺህ በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን ለማሰማራት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ሕብረት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከ3 ሺህ በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት አዘጋጅነት የሲቪክ ማህበራትና የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ተወካዮች የታደሙበት “ምርጫና ሰብዓዊ መብት” የተሰኘ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ 170 የሲቪል ማህበራትን ያቀፈው “የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ህብረት ለምርጫ” የተሰኘው ጥምረት አስተባባሪ አቶ አበራ ኃይለማርያም በዚህ ወቅት ለመገናኛ ብዙኀን እንዳሉት፤ ህብረቱ በግንቦት ወር የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ተዘጋጅቷል።

በዚህም በአገሪቱ 83 ዞኖችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በቅድመና ድህረ ምርጫ እንዲሁም በምርጫው ዕለት ታዛቢዎቹን እንደሚያሰማራ ነው የተናገሩት።

ከነዚህም መካከል በቅድመ ምርጫ 250፣ በምርጫ ወቅት ደግሞ 1 ሺህ 250 ተቀማጭና 500 ተንቀሳቃሽ የምርጫ ታዛቢዎች ይሰማራሉ።

የሲቪክ ማህበራት በምርጫ ወቅት የሚኖራቸው ሚና ከምርጫው በፊት፣ በምርጫ ዕለትና በድሕረ ምርጫ የሚኖሩ ቅሬታና አለመግባባቶች እንዲፈቱ ከ250 በላይ ታዛቢዎችን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ማህበራቱ ከታዛቢነት ባለፈም በምርጫ ትምህርትና ክትትል ላይ እንደሚሰራ አስተባባሪው ገልጸዋል።

ከምርጫው በፊት በአምስት ቋንቋዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ትምህርት ለመስጠት እንደተዘጋጀም ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ምንጭ፡-አልጀዚራወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.