Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በሩሲያ ውጭ  ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በሩሲያ ውጭ  ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ከአቶ ጂዮርጅ ቶዱዋ  ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አምባሳደር አለማየሁ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ስለተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ እየተከናወኑ ስላሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስላላት ወቅታዊ ግንኙነት የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ማደበር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.