Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 10 ሚሊየን ብርና የካቢኔ አባላቱ 50 በመቶ የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል፡፡
ካቢኔው በተጨማሪም በትግራይ ክልል ያለውን የጤና አገልግሎት ለመደገፍ ሁለት አምቡላንስ ተሽከርካሪ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታውቀዋል፡፡
አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ የሚገኙ ሶስት የብሄረሰብ ዞኖች በቀጣይ የሚችሉትን እንዲያደርጉ እንደሚሰራ ጠቅሰው÷ ክልሉን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ደረጃ የተዘጋጀው ድጋፍ ወደ ስፍራው የሚያደርስ የልዑካን ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ትግራይ ክልል እንደሚወሰድም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ክልሉን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.