Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን  ማህበረሰባዊ ቸልተኝነት በሚታይ ወቅት ህዝብን ማንቃታቸው ተገቢ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መገናኛ ብዙሃን ማህበረሰባዊ ቸልተኝነት በሚታይ ወቅት ህዝብን ማንቃታቸው ተገቢ ነው ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ኢቢሲ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች  የማስክ አጠቃቀም  ጋር በተያያዘ የሰራውን ፕሮግራም መነሻ በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት÷የመዲናዋ ነዋሪዎች የኮቪድ መከላከያ ማስክ ማድረግ ላይ ቸልተኝነት እያሳየን እንደሆነ በተገቢው አሳስቧል ሲሉ ገልጸዋል።

አያይዘውም ለጤናችን ዋጋ እንስጥ፣ ሁሌም ማስክ ማድረግ እንዳለብን አንዳንድ ጊዜ ለምንዘነጋ ሰዎች ጥሩ መልዕክት ነውም ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.