Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 51 ሺህ 700 የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 51 ሺህ 700 የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ትናንት የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጅጅጋ ወደ ሱማሌላንድ ሲጓዝ በተደረገ ፍተሻ 51 ሺህ 700 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳታወቀው ህገ-ወጥ ገንዘቡ የተያዘው ለቶጎውጫሌ ጉምሩክ መቆጣሪያ ጣቢያ በደረሰ ጥቆማ ነው፡፡
የተያዘው ገንዘብ በወቅታዊ ምንዛሪ 2 ሚሊየን 56 ሺህ 62 ብር ዋጋ አለው ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.