Fana: At a Speed of Life!

ብዘሃነታችንን በአግባቡ ይዘን ለኢትዮጵያን ብልጽግና መሠረት እንጥላለን- የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የአፋ መፍቻ ቋንቋ ቀን በሠመራ ከተማ እየተከበረ ነው።
የምክር ቤቱ አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ወቅት የቋንቋም ሆነ የአመለካከት እንዲሁም የባህል ብዘሃነታችን በአግባቡ መጠቀም ከቻልን ጠንካራ ሀገር በመፍጠር የብልጽግናን መሠረት እንጥላለን ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት የአፋር ህዝብ ባህልና ቋንቋ ተጠብቆ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቋንቋ እንዲሆን ተገቢውን በጀት በመመደብ የምርምር ማዕከል ከፍቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
አፋርኛ የክልሉ የመናገሪያ ቋንቋ ብቻም ሆኖ እንዳይቀር እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ድረስ የመማሪያ በመሆን የክልሉ ህዝብ በሀገራዊ የልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር አውላቸው ሹምነካ በበኩላቸው የአፍ-መፍቻ ቋንቋዎችን ማልማት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገትና ልማት ቁልፍ መሣሪያ በመሆናቸው በሁሉም ደረጃ ሊጠበቁ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩም ህገመንግስቱ ለቋንቋ ብዘሃነትን ከሠጠው እውቅና በተጨማሪ ብዘሃነቱን በአግባቡ ተቀብሎ ማስተናገድ የሚያስችል ሀገራዊ የቋንቋ ፖሊሲ ቀርጻ እየተንቀሳቀሰ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.