ስፓርት

14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ተካሄደ

By Meseret Awoke

February 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ከተማ ለ14ኛ ጊዜ ተካሄደ።

የሴቶች ውድድር ከማለዳው 1:30፣ የወንዶችም ደግሞ 1:45 ጀምሮ ተካሂዷል።

የሴቶችን ውድድር የድሬደዋ ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሣራ ሃሰን፤ የወንዶቹን ውድድር ደግሞ የድሬደዋ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ አስጀምረዋል።

ውድድሩም ተጠናቋል።

በሴቶች 1ኛ ሰንበሬ ተፈሪ ከፌዴ/ማረሚያ፣ 2ኛ ህይወት ገ/ኪዳን ከአልሚ ኦላንዶ፣ 3ኛ ፋታው ዘራይ ከኢት/ንግድ ባንክ፣ 4ኛ መሠረት ጎላ ከኢት/ኤሌክትሪክ፣ 5ኛ የኔነሽ ጥላሁን ከኦሮሚያ ክልል፣ 6ኛ በቀለች ጉደታ ከኦሮሚያ ክልል፣

በወንዶች 1ኛ ልዑል ገ/ስላሴ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ 2ኛ ሲሳይ ለማ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ 3ኛ በላይ ጥላሁን ከኢት/ንግድ ባንክ፣ 4ኛ ባለው ይሁኔ ከአማራ ፖሊስ 5ኛ ኃ/ማርያም ኪሮስ ከኢት/ኤሌክትሪክ፣ 6ኛ ፀጋዬ ጌታቸው ከኢት/ኤሌክትሪክ በመሆን አጠናቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!