የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

February 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

በውጭ ግንኙነት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባል በመሆን፤ በጤናው ዘርፍ ከድሆች ጓዳ የዘለቀ የህክምና ድጋፍ በመስጠት ሃገራቸውን በፅናት ያገለገሉት ታላቁ ምሁር እንደነበሩም አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሙያ አጋሮቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!