የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ሀዘኑን ገለጸ

By Meseret Awoke

February 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕክምና ሙያ፣ በሀገር ሽማግሌነት፣ በእርዳታ አስተባባሪነት እና በዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የነበሩት የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ሀዘኑን ገለጸ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!