ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በገበታ ለሃገር መረሃ-ግብር የኮይሻ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ዳውሮ ዞን ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በገበታ ለሃገር መረሃ-ግብር የኮይሻ ፕሮጀክትን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታን ለማስጀመር ዳውሮ ዞን ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዞኑ ሎማ ወረዳ ሲደርሱ የአካባቢው ህብረተሰብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡
በዋሩማ ቀበሌ ለሚገኘው እና የፕሮጀክቱ አካል ለሆነው “ንጉስ ሃላላ ካብ ክላስተር” የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ እና ከፍተኛ የፌደራል የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!