Fana: At a Speed of Life!

ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት ሳይፈፀምባቸው ወደ ሀገር ለማስገባት እና ከሀገር ለማስወጣት ሙከራ የተደረገባቸው ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በ13 የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስር በሚገኙ ኬላዎች የተያዙ ናቸው ብሏል፡፡

የጦር መሳሪያ (ፈንጅ፣ ሽጉጥ፣ የክላሽ ጥይት)፣ በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ ሀገር የሚገባ ነዳጅ፣ ጥራቱን ያልጠበቀ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ የምግብ ምርቶች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች (ብር፣ የአሜሪካን ዶላር፣ ድርሃም፣ የስዊስ ፍራንክ እና የሳውዲ ሪያል)፣ ማዕድን፣ የግብርና ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ከተያዙት መካከል መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.