የሀገር ውስጥ ዜና

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

February 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለአማራ ወጣቶች ማህበር አስረክቧል።

የስፖርት ክለቡ የሬዲዮ ክፍል ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ተወካይ አቶ ካሳሁን ደርቤ ሀገር መረጋጋት ስትጀምር ትውልድ መማር ስለሚቀጥል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም 50 ሺህ ደብተሮች እና ከ30 ሺህ በላይ እስክርቢቶና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለተቸገሩ ወገኖች እንዲደርስ በማሰብ ማበርከታቸውን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!