የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

February 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በቀጠናዊ እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ውይይቱም ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር በሚያጠናክሩባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበረም ጠቅሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!