ስፓርት

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ውድድር ከእሁድ ጀምሮ በድሬዳዋ ይካሄዳል

By Abrham Fekede

February 23, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ውድድር እና 14ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ከየካቲት 21 እስከ 27 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አስፋው ከትግራይ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡

“የባህል ስፖርቶቻችን ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ውድድር 11 የስፖርት ዓይነቶች ተካተውበታል፡፡

በውድድሩ የሀገር ገፅታ የሚገነባበት እንዲሁም የተሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማነታችው የሚለካበት እንደሆነ መግለጻቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በውድድሩ 576 ወንዶች፣ 253 ሴቶች በጥቅሉ 829 ስፖርተኞች እንደሚሳተፍ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን