የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በ2021 ሊከተሏቸው ከሚገቡ 14 የአየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ውስጥ ተካተቱ

By Abrham Fekede

February 23, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በ2021 ሊከተሏቸው ከሚገቡ 14 የአየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ውስጥ ተካተቱ።

አየር መንገዱ የሰብዓዊ እና ሌሎች የነፍስ አድን ድጋፎችን ለአህጉሪቷ አፍሪካና ሌሎች የዓለም ክፍሎች እያደረሰ ይገኛል።

አየር መንገዱ በአስደናቂ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት በማሳየት በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ሴንተር ኦፍ አቪዬሽን በጥር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በህዳር ወር የአስር ዓመት ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያስመዘገበው ትርፍም የስኬት መንገዱን ያሳየ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ይህንንም ተከትሎ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በ2021 ከሚጠበቁ 14 የአየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ውስጥ ሊካተቱ የበቁት ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን