Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን 4 ለ 3 አሸነፈ፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በ9፡00 ሰዓት በባህርዳር ስታዲየም አካሂደዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር ቀሪዎቹን አቤል እንዳለ እና አብዱልከሪም መሐመድ አስቆጥረዋል፡፡

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ28 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል 24 ነጥብ ሲኖራቸው በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ይከተላሉ፡፡

ጠዋት በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.