Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና በኬንያ ሰሞኑን የጣለው ዝናብ ለአንበጣ መንጋ መስፋፋት ዓይነተኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል – ፋኦ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡባዊ ኢትዮጵያና በሰሜናዊ ኬንያ ሰሞኑን የጣለው ቀላልና መካከለኛ ዝናብ ለበረሃ አንበጣ መንጋ መስፋፋት ዓይነተኛ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት/ፋኦ/ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ የዝናብ መጠኑ አነስተኛ መሆን እና መንጋውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በመጠናከሩ የከፋ አይሆንም ብሏል፡፡

ሁለቱ ሃገራት የበረሃ አንበጣ መንጋን በመከላከል ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውንም ድርጅቱ ጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል እና በደቡብ ክልል ኩብኩባዎች መታየታቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በደቡባዊ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ እንደነበርም ነው የጠቀሰው፡፡

በኬንያ፤ በሶማልያ በኩል የሚመጣው መንጋ ቢያቆምም በመጠን አነስተኛ የሆነ ኩብኩባ መከሰቱን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡

በሶማልያ አዳዲስ ኩብኩባዎች መከሰታቸው የተሰማ ሲሆን ይህም ወደ ኢትዮጵያና ወደ ኬንያ ሊዛመት እንደሚችል ድርጅቱ ጠቅሷል፡፡

ዘንድሮ በምስራቅ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ባለፉት ዓመታት ካለው እንደሚለይ የገለጸው ድርጅቱ፤ የአንበጣ መንጋ የመከላከል ሂደቱ መጠናከሩንም አንስቷል፡፡

የአንበጣ መንጋውም ከዚህ ቀደም እንዳለው የሰፋ ያለመሆኑን ጠቅሶ እንቁላል የሚጥሉበት ደረጃ ላይ አልደረሱም ሲል ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.