ኮሮናቫይረስ

በኮቫክስ እገዛ የተደረገበት መጀመሪያው የኮቪድ 19 ክትባት ጋና ገባ

By Abrham Fekede

February 24, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኮቫክስ እገዛ የተደረገበት የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጋና ደርሷል፡፡

ኮቫክስ ለጋና 600 ሺህ መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ነው ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቀው፡፡

ክትባቱ በበብሪታንያ የበለጸገው ኦክስፎርድ አስራዜኒካ ክትባት ነው ተብሏል፡፡

ጋና የኦክስፎርዱን አስራዜኒካ ክትባት ስትቀበል ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች፡፡

በቀጣይ ቀናትም የመጀመሪያ ዙር የክትባት ድጋፎች እንደሚቀጥሉ በአፍሪካ ቀጠና የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን