Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የአድዋ በዓል በባህርዳር ከተማ ከየካቲት 19 እስከ 23 ይከበራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የአድዋ በዓል በባህርዳር ከተማ በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከየካቲት 19 እስከ 23 በድምቀት እንደሚከበር ተገለጸ፡፡

በዓሉ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በሚቀርብ ፓናል፣ በሙሉዓለም ባህል ማዕከል አዘጋጅነት አድዋን የሚዘክሩ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

እንዲሁም “ለንግስቲቱ እጓዛለሁ” በሚል መነሻ የእግር ጉዞ በየካቲት 21 ይካሄዳል

ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የካቲት 23 ደግሞ በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ የአባት አርበኞች በተገኙበት የፈረስ ጉግስ ትዕይንት ፣የነጋሪት ጉሰማ፣ የአዝማሪዎች የማሲንቆ ጨዋታ፣ ታላላቅ አርቲስቶች የሚታደሙበት እምቢልታ የመንፋት ትርኢት፣ የአድዋ ዘማቾችን ተጋድሎ ለትውልድ ለማሻገር በስማቸው መንገዶችን ሰይሞ መዘከር እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

በዚህ ህዝባዊና ታሪካዊ የሆነው የአድዋ በዓል በከተማችን በድምቀት ሲከበር የባህርዳር ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ፣ የክልል እና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ተጋባዥ እንግዶች እና ሌሎች ኃላፊዎች እንደሚታደሙ ከባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መላው ኢትዮጵያውያን በአድዋ ድል ለግል ጥቅም ሳይሆን ለሀገር አንድነት መሰዋትን ለብሔርተኝነት ሳይሆን ለሰብዓዊነት መቆምን፤ ከዚህ ባለፈም ለዓለም ጥቁር ህዝቦች መብት መከበር እና ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ልዕልና ሲባል ከአዕምሮ የማይጠፋ ታሪክ መሰራቱን በማንሳት የሚዘክርበት ልዩ በዓል መሆኑንም ነው የተጠቀሰው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.