Fana: At a Speed of Life!

በቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመራ ልዑክ  ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል፡፡

ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋም ተገኝተዋል፡፡

ለልዑኩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድና ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡

አቶ ኃይለማርያም በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ድንቅ የተፈጥሮ ሀብት የሆነው የባቢሌ የዝሆኖች ፓርክ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ብርቅዬ ዝሆኖች እንዳይጠፉና እንዳይመናመኑ የተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚሰራ ፋውንዴሽን መስርተው እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ይህንን የባቢሌ የዝሆኖች ሀብትን ለመንከባከብ እና ለመታደግ ስራዎችን ለመስራት ወደ ጅግጅጋ ማቅናታቸውን የገለጹት አቶ ኃይለማርያም፣  ፋውንዴሽናቸው በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሁለቱ ክልል አመራሮች ጋር  እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በነገው ዕለትም በዱር እንስሳት ጥበቃ ዙሪያ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኀን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.