Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ከየካቲት 9 ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት መመለሱን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ ሌሎች ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ እየተሰራ ሲሆን፤ ከሰሞኑ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

የህወሓት ጁንታ ርዝራዦች አዲጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ – መኾኒ – መቐለ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረሱት የማበላሸት ተግባር በመላው ትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጹ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.