Fana: At a Speed of Life!

የኦማን ሱልጣን ቃቡስ ቢን ሰኢድ አል ሰዒድ በ79 ዓመታቸውአረፉ 

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓረቡ ዓለም በመሪነት ረዥም ጊዜ በመቆየት ቀዳሚው የኦማኑ ሱልጣን  ቃቡስ ቢን ሰኢድ አል ሰዒድ በ79 ዓመታቸው ማረፋቸው  ተሰማ

ሱልጣን  ቃቡስ ቢን ሰኢድ አል ሰዒድ  የካንሰር ታማ ሚ   እንደነበሩ የተነገረ ሲሆን፥  በቤልጂየም ህክምና ሲከታተሉ ነበር ተብሏል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1970 ደም ሳይፈስ በእንግሊዝ ድጋፍ አባታቸውን ከስልጣን በመፈንቀል ነው ሱልጣን  ቃቡስ ቢን ሰኢድ አል ሰዒድ ወደ መሪነቱ የመጡት።

ቃቡስ ቢን ሰኢድ ኦማንን  መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ሀገሪቱ ፈጣን እና ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባ ወደ ብልጽግናው ጎዳና አምርታለች።

ኦማን ከአሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ጋር ጠንካራ ወዳጅነት እንድትመሰርትም አድርገዋል።

ትዳርና ልጅ የሌላቸው ሱልጣን ቃቡስ ቢን ሰኢድ ወራሻቸውን ከህልፈታቸው በፊት ባያዘጋጁም በኑዛዜያቸው መሰረት፣ የቀድሞው የባህል እና ቅርስ ሚኒስትር ሀይሰም ቢነ ጧሪቅ በምትካቸው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.